የሀዋሳ ግብርና ምርምር ማዕከል በሀዋሳ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ በማንሳት ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ዛሬ 22/12/2013 ዓ.ም ሰጠ፡፡

በሀዋሳ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ በማንሳት ስራ ላይ የተሰማሩ ባለጋሪዎች ለኮቪድና-19ና ለተዛማጅ በሽታዎች ያላቸዉን ተጋላጭነት ላማስቀረት የሀዋሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ወጣቶችንና እና የተለያዩ ባለድረሻ አካላትን በመጋበዝ ስለበሽታዉ አስከፊነትና መደረግ ስለሚገባዉ ጥንቃቄ ለወጣቶቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ስቷል፡፡
የስልጠናዉ አዘጋጅ እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር አማረ አርጋው የእንኳን ደናመጣችሁ መልክታቸዉን በማስተላለፍ የደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲቱት የፋይናስ ዘርፍ ዳሬክተር የሆኑትን አቶ ታምራት ተሰማ የመክፍቻ ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዟቸዋል፡፡
አቶ ታምራትም ወጣቶቹን ለሀዋሳ ከተማ ጽዳት ከፍተኛዉን ሚና እየተጨወቱ መሆናቸዉን ገልጸዉ የተዘጋጀዉም ፕሮግራም ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጠው እምነታቸዉን በመስጠት በመደራጀትና በተናጠል ስራዉን የምትሰሩ ወጣቶች በዚህ ስልጠና እጅግ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ትኩረት ስጡት ብለዋል አያይዘዉም በከተማዋ የሚኖር ሕብረተሰብ ጤናማ እንዲሆን ለማድረግ የጸዳ ከተማ ከምንም በላያ አስፈላጊ ነዉ ሲሉ ለወጣቶች እራሳቸዉን ከበሽታ መጠበቅ እንዳለባቸዉና ስራቸዉን በስነ-ምግባር በማነጽ ና የከተማዋን ዉበት በጠበቀ መልኩ ስራቸዉን መስራት እንዳለባቸዉ በመምከር ስልጠናውን አስጀምረዋል፡፡
የፕሮጀክቱ አስተባባሪና ዶ/ር አማረ አርጋው በስልጠናዉ ላይ እንደተናገሩት የሀዋሳ ከተማ በስምንት ክፍለ ከተማ የተዋቀረና በአገራችን ከሚገኙ እጅግ ፅዱ እና ውብ ከሚባሉ ለኑሮ ምቹ ከሆኑ ከተሞች አንዷ መሆኗን እና ለዚህም ፅዱነት አስተዋፅሆ እያደረጉ ካሉት የደረቅ ቆሻሻ አንሺ ወጣቶች በዋነኝነት ተጠቃሽ ናቹ በማለት ፡ባለጋሪዎች በየቀኑ በየክፍለ ከተማዉ ተሰማርተዉ ቤት ለቤት እየዞሩ ቆሻሻ የማንሳት ስራ እየተገበሩ መሆናቸዉና በቆሻሻ አሰባሰብ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች በቁጥር ከ200 መቶ የሚበልጡ ስሆን አብዛኛዎቹ ከ12 ዓመት እስከ 25 ዓመት እድሜ ክልል የሚገኙ መሆናቸዉና እነሱ ባይኖሮ በመዘጋጃ አቅም ብቻ የከተማዋን ደረቅ ቆሻሻ በሙሉ ማንሳት የማይችል መሆኑን በመግለፅ ነገር ግን በኮቪድ 19ና ሌሎች ተዛማጅ በሽታ ላይ ትኩረት ያልተሰጣቸዉ እንደነበረ በመግለጽ ክፍተቱን ለመሙላት የሀዋሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ፐሮጀክት በመጻጻፍ ይእን ስልጠና ያዘጋጀ መሆኑን ገልጸዉላቸዋል፡፡
ከሀዋሳ ጤና አጠባበቅ የተጋበዙት ባለሞያ ሰለ ኮቪድ -19 ና ስለ ተዛማጅ በሽታ አስከፊነት ና መደረግ ያለበት ጥንቃቄ በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰተዋል፡፡በስተመጨረሻም በስልጠናው ዙሪያ አስተያየት ከወጣጦቹና ከባለድርሻ አካላት በመቀበልና ምላሽ በመስጠት ጠናቋል፡፡

May be an image of 2 people, people sitting and indoorMay be an image of 1 person and standingMay be an image of 1 person, standing and indoorMay be an image of 4 people, people sitting and indoorMay be an image of 6 people, people sitting and indoor

Hits: 1367