በቆሎና ቦለቄን አሰባጥሮ በመዝራት የበቆሎንና የቦለቄን ምርት መገምገም

Written by Super User

በቆሎና  ቦለቄን  አሰባጥሮ  በመዝራት የበቆሎንና የቦለቄን  ምርት መገምገም 


ቦለቄ  በዋነኝነት ከቦቆሎ፤ ማሽላና ስራስር ሰብሎች(እንሰትና ጎደሬ) ጋር አሰባጥሮ መዝራት ይቻላል፡፡ በቆሎን ከቦለቄ ጋር አሰባጥሮ በመዝራት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች  ይገኛል ከነዚህም  ውስጥ በተወሰነ የእረሻ ቦታ ብዙ ምርት ለማግኘት ፤ የአፈር ለምነትን ለመጨመር ማለትም ከአየር ናይተሮጅንን በመጠቀም አፈር ውስጥ በማስቀመጥ ለራሱና ለቀጣይ ሰብል ይጠቅማል፤ በሽታዎችን እና አረሞችን ለመቀነስ  ከፍተኛ  ጥቅም ያስገኛል፡፡ በደቡብ  ኦሞ ዞን የተወሰኑ አርሶ አደሮች አሰባጥሮ መዝራት የተለመደ ቢሆንም የስብጥር  አሰራር ግን  በመስመር የመዝራት  ላይ መሰረት ያደረገ  አይደለም፡፡ ስለዚህ አርሶ አደሩ ባለው የእርሻ መሬት ውስንነት ምክንያት በቆሎንና ቦለቄን  አሰባጥሮ በመስመር በመዝራት  ምርቱን   ማሳደግ የሚችልበት የተሻሻለ የአመራረት  ቴክኖሎጂ ለመጠቀም  እና ለማስተዋወቅ የበቆሎንና የቦለቄን በማሰባጠር  በምርታማነት ያለዉ ተጽኖ የመለየት ስራ ተከናዉነዋል፡፡

 

 በቆሎና  ቦለቄን  አሰባጥሮ  በመዝራት  ከበቆሎና  ከቦለቄ 

የተገኘ  ምርትና  የምርት ዋጋ

ተ.ቁ

የስብጥር ሥርዓቱ

የምርት መጠን (ኩል / ሄር

                አዋጭነቱ

በቆሎ

ቦለቄ

(land equivalent ratio)

የምርት ዋጋ (ብር/ኩንታል)

1

1 መስመር መቆሎ 2 መስመር ቦለቄ

55.5

17.2

1.5

35 ,960

2

1 መስመር መቆሎ 1 መስመር ቦለቄ

43.3

26.4

1.66

38,440

3

በቆሎ  ብቻ

61.1

-

-

24,440

4

ቦለቆ   ብቻ

-

27.2

-

21,760

 1. በደቡብ  አሪ ወረዳ አይካመር ቀበሌ የበቆሎና  ቦለቄ  አሰባጥሮ  መዝራት  በማሳ  ላይ  

ማጠቃለያ

በቆሎንና ቦለቄን አሰባጥሮ በመዝራት በቆሎው በቦለቄው ላይ ወይም ቦለቄው በቆሎው ላይ ምንም አይነት ተጽኖ እንደማያደርስበት የተሰራው የምርምር ውጤት ያሳያል፡ ይህም ማለት በቆሎና ቦለቄ ተሰባጥረው ሲዘሩ መቆሎ ብቻ ይመርተው የነበርው መሬት ቦለቄ ተጨማሪ ምርት ያስገኛል፡ ስለዚህ በቆሎ  ወይም ቦለቄ ብቻውን ዘርቶ ከማምረት ይልቅ  በቆሎን ከቦለቄ ጋር አሰባጥሮ በመዝራት ምርትን  መጨመር ይቻላል፡፡ 1(አንድ) መስመር በቆሎ  1(አንድ) መስመር ቦለቄ በመዝራት ምርትና የምርት ዋጋን  በመጨመር  ተጠቃሚነትን  ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

2. የድቡልቡል  ድንች የዝርያ ማላመድ ሙከራ
መግብያ
ድንች በኢትዮጵያ ከሚመረቱት  የስራ ሰር ሰብሎች አንዱ ና ዋነኛው ሲሆን በበርካታ የአገሪቱ ክፍሎችም በሰፊው ይመረታል:: ድንች በሃገራችን በዋናነት ለምግብነትና ለገቢምንጭነት በከፍተኛ ደረጃ ጥቅም ላይ ይውላል:: በደቡብ ኦሞ ዞን  በደጋና በወይና ደጋው አካባቢ በሰፊው የሚመረት የስራስር  ሰብል ቢሆንም በአርሶ አደር የሚገኙት ዝርያዎች  ምርታማነታቸዉ እና በሽታ የመቋቋ አቅማቸዉ አነስተኛ በመሆኑ አምራች አርሶ አደር ሰብሉ ካለዉ  የምርታማነት ዓቅም ማግኘት የሚገባዉ ምርት እያገኙ አለመሆኑ የተደረገዉ የዳሰሳ ጥናት ዉጤት ያመለክታል፡፡ በመሆኑም በሽታ በመቋቋም ክፍተኛ ምርት መስጠት የሚችሉ እና ለአከባቢዉ ተስማሚ የሆኑ ዝርያዎች ለመለየት ይህ የምርምር ተግባር ተከናዉነዋል፡፡

የተገኙ  የምርምር ውጤቶች

ሰንጠረዥ 1. የተለያዩ የድብልብል ድንች  ዝርያ ማላመድ ሙከራ

ተ.ቁ

የዝርያች  ስም            

የተገኘ የምርት መጠን (ኩንታል/ሄክታር)

1

በለጠ

140

2

ጃለኒ

136

3

ጉደኒ

27.8

4

የአካባቢ ዝርያ

58.9

 በደቡብ  አሪ ወረዳ  ሰልማመር  ቀበሌ የተለያዩ  የድብልብል  ድንች  ዝርያ ማላመድ ሙከራ 

ማጠቃለያ

በዚህ የማላመድ ሙከራ 3 የተሸሻሉ ዝርያዎች እና አንድ በአርሶ አደር የሚመረት ዝርያ በማወዳደር ለአከባቢዉ በሽታ በመቋቋ የተሸለ ምርት የሚሰጡ ዝርያዎች የመለየት ስራ በመከናወን ከአከባቢ ዘር አንጻር በለጠ ዝርያ ከፍተኛ ምርት ሰጥተዋል፡፡ ከአከባቢ ዘር ሲነጻጸር በ81ኩ/ል በሄር በመብለጥ የተሸለ ሆኖ ተመርጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ዝርያ በሌሎች አከባቢዎች ከሚሰጠዉ ምርታማነት አንጻር አነስተኛ በመሆኑ ሌሎች የአመራረት ዘዴዎች በመቀመር ለአርሶ አደር መድረስ እንዳለበት በጥናቱ ተወስነዋል፡፡

ለዝናብ አጠር አከባቢ የማሽላ ዝርያዎች ማላመድ እና ማስተዋወቅ ሙከራ


መግብያ


ማሽላ በኢትዮጵያ ከሚሸፍነው መሬት ስፋትና ከጤፍና ከበቆሎ ቀጥሎ በ3ኛ ደረጃ የሚገኝ ሲሆን በምርታማነት ደግሞ ከበቆሎ፣ ስንዴና ሩዝ ቀጥሎ በ4ኛ ደረጃ ይገኛል፡፡ አገራዊ አማካይ የምርት መጠን ከአለም አቀፍ የማሽላ ምርታማነት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ ለዚህ ዝቅተኛ የማሽላ ምርታማነት የተሻሻሉ ዝርያዎችና የአመራረት ዘዴዎች በመጠቀም ምርታማነት መጨመር ተችሏል፡፡ በመሆኑም በዞናችን ላሉት ዝናብ አጠር አከባቢዎች የተሻሻሉ ምርጥ ዝርያዎች የማላመድ እና የማስተዋወቅ በተሰሩት ስራዎች ከአከባቢ ዝርያዎች የተሸለ ምርታማነት የሚሰጡ ዝርያዎች ተለይተዋል፡፡

በአልዱባ ቀበሌ በተከታታይ ለ2 ዓመት የማሽላ የማላመድ ሙከራ በመከናወን የተገኘ አማካይ ምርታማነት

የዝርያ ስም

ምርት ለመሰብሰብ የወሰደበት ጊዜ (በቀን)

የተገኘ ምርት በኩ/ል

ተሸለ

122

19.42

መልካም

113

17.18

ጋምቤላ-1107

119

11.58

ESH1

114

11.47

76T123

115

10.85

የአከባቢ ዘር

135

9.13