የደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩና በሥሩ የሚገኙ የምርምር ማዕከላት ማናጅመንት አባላት ከመስከረም 20/2013 ጀምሮ እያደረገ ባለው ስብሰባ  ለ2013 በጀት ዓመት በክልል መንግሥት የተመደበውን  ካፒታልና መደበኛ በጀት የየምርምር  ማዕከላት የማናጅመንት አካላት ጋር በመሆን ክፍፍል አድርጓል፡፡ የበጀት ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ለመፍጠር መንግሥት ካሰቀመጠው አቅጣጫ የታችኛውን እርከን ማጠናከር ስለሚገባና የተገኘ ሀብት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ከተፈቀደው በጀት ውስጥ ከ7% እስከ 10% በክልል ማዕከል ደረጃ በማስቀረት የቀረውን 90% ለምርምር ማዕከላት ተደልድሏል፡፡ በ2013 በጀት ለኢንስቲትዩቱ መደበኛ በጀት ብር100,652,073 ካፒታል 36,148,640  በድምሩ 136,800,713 ብር የተመደበ ሲሆን፡፡  በስተመጨረሻም ከየማዕከላቱ በተነሱ ጥያቄዎቸና   አስተያየቶች ላይ የኢንስቲትዩት  ዳሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል ምላሽ የሰጡ ሲሆን  የ2013 በጀት ከአምናው ብዙ ቀንሶ የመጣ ስለሆነ በ2012 የተጀመሩ የምርምር ሥራዎችን በሚደግፍ መልኩ እንዲሠራና ተሻጋሪ ሥራዎች ግን እየታዩ ተግባራዊ እንዲደረጉ አቅጣጫ በማስቀመጥ መጭዉ የስራ ዘመን  የብልፅግናና የስራ የዕድግት እንዲሆን ምኞታቸዉን በመግለጽ  ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

DSC 0033099

DSC 003902DSC 004503DSC 005306DSC 005406