ሙስና አለም አቀፍ እና ሀገር  አቀፍ ችግር መሆኑ  ከተረጋገጠ  ዘመናት  ተቆጥሯል ፡፡በፀረ-ሙስና  ትግል ዉጤታማ  የሆኑ ብዙ ሀገራት ለስኬት ካበቃቸዉ የሙስና ና ብልሹ ተግባራት መከላከያ  ስልቶች  መካከል  የፈጠራቸዉ እና ተግባራዊ ያደረጋቸዉ የትብብር የቅንጅት ስራዎች ዋነኛዎቹ ናቸዉ ፡፡ሙስና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል በአንድም ይሁን በሌላ መልክ ከሚንቀሳቀሱ መሰል ተቋማት ጋር መቀናጀት እጅግ አስፈላጊ ነዉ፡፡ስለሆነም

በዘንድሮዉ ዓመት የሚከበረዉ የፀረ-ሙስና ቀን ተቋማት ሙስናን  ብልሹ አሰራርን በጋራ ለመከላከል ሊኖረዉ የሚገባዉ የትብብር ና የግንኙነት ስርዓት ይበልጥ ለማጠናከር የምናድስበት እለት ሊሆን ይገባል፡፡

ዘንድሮም የሚከበረዉ  በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ግዜ፡ በሀገራችን  ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ እንዲሁም በክልላችን  ለ15ኛ ጊዜ “የትዉልድ  የሥነ -ምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲስፕልን በመምራት ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመታገል የብልጽግና ጉዟችንን እናፋጥናለን !!! ”በሚል ቃል  ህዳር 18 /2013 ዓ.ም   የደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት  አመራሮችና ሠራተኞች  በስልጠናና  በዉይይት  ቀኑ ተከብሮ ዉሏል፡፡

 DSC 0064DSC 0050

DSC 0043DSC 0037

DSC 0035