የአለም ኤድስ ቀን በያመቱ የማክበር አላማ ሀገራት እንዲሁም ህዝቦችን በየጊዜዉ የበሽታዉን አሳሳቢነት በመገንዘብ የአሰራር ስልቶቻቸዉን እያሻሻሉ ስለ እሁነታዉ በግልጽ እየተወያዩ ህዝብን ከበሽታዉ ስርጭት ማዳንና ለወደፊት ከቫይረሱ ነፃ የሆነ ትዉልድን ለማፍራት ነዉ፡፡

በአለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ኤችአይቪ በደማቸዉ ለሚገኝባቸዉና በቫይረሱ ጉዳት ለደረሰባቸዉ ወገኖች ድጋፋቸዉን ለማሳየት እንዲሁም በኤድስ ህይወታቸዉን ያጡትን ወገኖች ለማስታወስ በዓመቱ ህዳር 22 ቀን የዓለም ኤድስ ቀን ተከብሮ ይዉላል ፡፡

እ.ኤ.አ በ2020 የዓለም ትኩረት -19 ወረርሽኝ በጤና ፡ በህወትና   በኑሮ እያስከተለዉ ባለዉ ተፅዕኖላይ አርፏል ፡፡የኮቪድ -19 ወረርሽን ጤና ከሌሎች ትኩረት   ከሚሹ ጉዳዮች ለምሳሌ፡-እኩልነት ከማሰፈን፡ከሰብአዊ መብቶች ፡ከፆታ እኩልነት ፡ከማህበራዊ ጠበቃና ከኢኮኖሚ ዕድገት ጋር እንዴት ጠንካራ ቁርኝነት እንዳለዉ እሳቶናል ፡፡ይህንን ከግምት ዉስጥ በማስገባት በዚህ ዓመት የዓለም ኤድስ ቀን “ ኤችአይቪን   ለመግታት ፡አለምአቀፋዊ ትብብር   ፡የጋራ ኃላፊነት” በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡ የደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት እና የሀዋሳ ማህከል ሰራተኞች በጋራ የዓመቱን የኤችአይቪ ቀንን በደመቀ ስንስራት አከበሩ፡፡