የደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የካቲት 8/2013 ዓ.ም ዓመታዊ የምርምር ሥራዎች ዕቅድ ግምገማ ዐውደ ጥናት በቡታጅራ ከተማ  የጀመረ ስሆን በፈደራል የምርምር ተቋማትና በዩንቨርስቲዎች እየተሰሩ ያሉና ልሰሩ ታቀዱ የምርምር ሥራዎች ቀርበዉ በባለድርሻ አካላት ዉይይትና ምክክር የተደረገ ተደርጓል፡፡እንድህ አይነቱ መድረክ የምርምር ስራ ድግግሞሽና የሀብት ብክነትን በማስቀረት የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች በቅንጅት ለመስራት  ምቹ መደላድል እንደፈጠረና ቀጣይነት ያለዉ እንደሆን በመግባባት የተጠናቀቀ ስሆን ፡-

ዛሬ የካቲት 9/2013 ዓ.ም  አቶ አንተነህ ፈቃዱ በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና  እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት  ቢሮ ኃላፊ ፤ አቶ መሃመድ ጀማል የጉራጌ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ፤የደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት  ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አግደው በቀለ እና የኢትዮጵያ ግብረና ምርምርና የብሔራዊ ግብርና ምርምር ካዉንስል ከፍተኛ ተመራማሪዎች  በተገኙበት ዓመታዊ  የምርምር የስራ አፈጻጸም ግምገማ በይፋ ተጀምሯል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳሬክተር  በሰብል፤በተፈጥሮ ሀብት ፤በእንስሳት እንድሁም በሌሎችም የምርምር ዘርፎች ዓመታዊ የምርምር ሥራ ግምገማ የሚካሄድ መሆኑን ጠቅሰዉ የግምገማ ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን  ሁሉም ተመራማሪዎች ላፊነታቸዉን በአግባቡ እንዲወጡ በማሳሰብ  የጉራጌ ዞን ምክትል ዋና  አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እንዲያስተላልፉ ጋብዘዋል ፡፡

አቶ መሃመድ ጀማልም የምርምር ውጤቱ ለአርሶ አደሩ እያደረገ ያለዉ አስተዋጽዎ እጅግ ከፍተኛ  መሆኑን ገልጸው ከወልቅጤ በ111 ኪሎ ሜትር በምትርቀው በቡታጅራ ከተማ ይህንን የዓመታዊ የምርምር ሥራዎች  ግምገማ ለማድረግ  እንኳን ደህና መጣችሁ  በማለት ቡታጅራ ከተማን ለዚህ ስብሰባ ስለመረጣችኋት እናመሰግናለን ብለው  በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና  እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት  ቢሮ ኃላፊ የሆኑትን አቶ አንተነህ ፈቃዱን  ጋብዘዋል፡፡

አቶ አንተነ ፈቃዱ  ባስተላለፉት  መልዕክት ምርምሩ እስካሁን የመጣበት ሂደት እንደ አገር መልካም ቢሆንም በቀጣይ የግብርና ምርትና ምርታማነት ለመጨመር አሁን ከመጣንበት በላይ መስራት እንዳለበት ገልጸው አሁንም አገራችን ኤክስፖርት ከማድረግ ይልቅ የግብርና ምርቶችን ኢንፖርት የምታደርግ   በመሆኑ ይህን ችግር ለመቅረፍ ከምርምር ዘርፉ ከፍተኛ ስራ እንደሚጠበቅ በመጠቆም የውይይቱ ቆይታ ፍሬያማ እንደሚሆን እምነታቸዉን ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም  ተመራማሪዎች በየዳይሬክቶረቱ  በመከፋፈል የምርምር ስራ ግምገማቸዉን ቀጥለዋል፡፡